አምላካችን ቅዱስ ነው

አምላኝችን ቅዱስ ነህ
ፊጣሪያችን ቡሩክ ነህ
የዘለዓለም አምላክ ነህ
የአዳም ልጅ ከትቢያ ወደ ነበረበት
መልሶም ከአፈር እንዲሆን ከመሬት
በተናገርከው ቃል ባዘዝከው መሠረት
እንደ ገአርፍ መጥተህ ትወስዳለህ ድንገት
ከሕልም የረዘመ ሕይወት የለንም
ማለዳ እንደሚበቅል እንደ ጠዋት አረም
ጠውልገአ እንደሚቀር እንደ ጠዋት አረም
ሕይወትህ ናትና እንደ ጠዋት ጠ?ዛ
ረግፎ ለሚቀር ውበትና ለዛ
እባክህ የሰው ልጅ ኃጢአትን አ ብዛ
ዕድሜያችን ሰባ ዓመት ቢበዛ ሰማንያ
በመከራ ያልቃል እርሱም በዓለም ዙሪያ
እኛም እናልፋለን በጭራሽ ሳንሠራ
በራስ ተሸክመን የኃጢአት አዝመራ
የመከራ ዓመ ት አሳልፈናል
ፍርድህን በመፍራት ተሸብረናል
እባክህ ጌ ሆይ በችሮ ህ ሥራ
ለአገልጋዮችህ አምላክ ሆይ ራራ
← መዝሙር