አምላኬ ሆይ አትተወኝ ፈጣሪዮ ተመልከተኝ
✦
አምላኬ ሆይ አትተወኝ ፈጣሪዮ ተመልከተኝ፪
ምንም ብበድልህ የእጆችህ ሥራ ነኝ
በዓለም ፍላጎት ታሥሬ እንዳልጠፋ
አውጣኝ ከፈተና አንተው ሆነኝ ተስፋ
አዝ.
ሥጋዊ ፈቃዴ ተበረታቶ ነፍሴ እጅጉን ተዳክማለች፪
የእጆችህን ማዳን ተስፋ ታደርጋለች
አዝ.
የሞትክልኝ አምላክ መድኃኒት ሆነህ መድኃኒት አንተ ለኔ፪
እንዳይሠለጥኑብኝ ፍዳና ኩነኔ
አዝ.
በሥጋህ በደምህ የገዛⷐኝ የዋጀⷐኝ ጌታ፪
ኃይል የለኝምና ሁንልኝ መከታ
አዝ.
ምንም ብበድልህ የእጆችህ ሥራ ነኝ
በዓለም ፍላጎት ታሥሬ እንዳልጠፋ
አውጣኝ ከፈተና አንተው ሆነኝ ተስፋ
አዝ.
ሥጋዊ ፈቃዴ ተበረታቶ ነፍሴ እጅጉን ተዳክማለች፪
የእጆችህን ማዳን ተስፋ ታደርጋለች
አዝ.
የሞትክልኝ አምላክ መድኃኒት ሆነህ መድኃኒት አንተ ለኔ፪
እንዳይሠለጥኑብኝ ፍዳና ኩነኔ
አዝ.
በሥጋህ በደምህ የገዛⷐኝ የዋጀⷐኝ ጌታ፪
ኃይል የለኝምና ሁንልኝ መከታ
አዝ.
✦