አንቺ የወይን ሐረግ

አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ
ምግብ ሆኖ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ
ኸኸ
በአንቺ ሰማይነት ድንግል የወጣው ፀሐይ
ብርሃን ነው ለጻድቃን ስሙም አዶናይ ኸኸ
ፊደል ትመስያለሽ ድንግል ወንጌል ትወልጃለሽ
ለመላእክት የማይቻል ነበልባሉን የቻልሽ ኸኸ
የመሶብ ምሳሌ ድንግል የኮከብ መገኛ
በሥጋችን በነፍሳችን እንዳንራብ አንቺ አለሽን ለእኛ ኸኸ
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ 22/
ምግብ ሆኖ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ ኸኸ
← መዝሙር