አንቺን የያዘ ሰው

አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ
በረከትሽ ብዙ የደናግል ገንዘብ
የምስኪናን እናት የርኁባን ቀለብ
ለሁሉ መጋቢ ጸጋሽ የማይጎድል
ስምሽ ጥዑም ምግብ ከረሀብ የሚያስጥል
አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ
አንቺ ብትመጪ ከምስኪኗ ቤቴ
እንደ መጥምቁ እናት በዛልኝ ሐሴቴ
የአዲስ ኪዳን ቁርባን መንበር ጠረጴዛ
ጽድቅን አሸተትን የሕይወት መዓዛ
አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ
ልቤ ተጠራጥሮ ኪዳንሽን ካልከዳ
ልመናም አልወርድም አልይዝም አኩፋዳ
ሁሉን እየሞላሽ መመገብ ታውቂያለሽ
ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋና ሃብት አለሽ
አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ
የእግዚአብሔር ማረፊያ ኮሬባዊት ዋሻ
የሕይወት ውሃ ምንጭ የህግ መፍሰሻ
ነበልባል ተዋሕዶሽ ሙሴ አንቺን አይቷል
ጫማውን አውልቆ በፊትሽ ተደፍቷል
አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ
← መዝሙር