አንድ ጊዜ
✦
አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ሆኛለሁ፪
በፍቅሩ ተስቤ በደሙ ድኛለሁ
ዓለም ተይኝ ንቄ ትቼሻለሁ
ጥበበኛው ሰይጣን በመጣው ቢመጣ
ዳግም ተመልሼ ከእቅፍህ ላልወጣ
በመስቀሉ ግርጌ አርፌ እኖራለሁ
ዓለም ተይኝ የእግዚአብሔር ሆኛለው
አዝ ---
ቢያሙኝ ቢያጥላሉኝ ቢሳለቁብኝ
ውርደትን ተንኮልን ቢሸርቡብኝ
ለእኔ እንደው ደስታ ነው ሐዘንም የለኝ
ሰይጣን እፈር የክርስቶስ ነኝ
አዝ ---
ጓደኞቼ ጠሉኝ ተለውጬባቸው
የጥንቱን ፀባዬን ስለነፈግኹአቸው
ብቻዬን የሆንኩኝ ቢመስለኝም ለእኔ
ጌታ እንደሆን አለልኝ ከጎኔ
አዝ ---
በፍቅሩ ተስቤ በደሙ ድኛለሁ
ዓለም ተይኝ ንቄ ትቼሻለሁ
ጥበበኛው ሰይጣን በመጣው ቢመጣ
ዳግም ተመልሼ ከእቅፍህ ላልወጣ
በመስቀሉ ግርጌ አርፌ እኖራለሁ
ዓለም ተይኝ የእግዚአብሔር ሆኛለው
አዝ ---
ቢያሙኝ ቢያጥላሉኝ ቢሳለቁብኝ
ውርደትን ተንኮልን ቢሸርቡብኝ
ለእኔ እንደው ደስታ ነው ሐዘንም የለኝ
ሰይጣን እፈር የክርስቶስ ነኝ
አዝ ---
ጓደኞቼ ጠሉኝ ተለውጬባቸው
የጥንቱን ፀባዬን ስለነፈግኹአቸው
ብቻዬን የሆንኩኝ ቢመስለኝም ለእኔ
ጌታ እንደሆን አለልኝ ከጎኔ
አዝ ---
✦