አንድ ቀን አለ
✦
አንድ ቀን አለ የሚያስፈራ ለጻድቃን የሚያበራ፪
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል በክበሩ ይገለጻል፪
አብረው ከእርሱ ጋር ይመጣሉ ቅዱሳን መላእክት ሁሉ፪
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል በዙፋን ይቀመጣል፪
የምሕረት አዋጅ ይታወጃል ነፍስ ሁሉ ይጨነቃል፪
ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ በግራው ይቆማሉ፪
ቅዱስ ቃሉን ሰምተው ያመኑ የጸኑ በኪዳኑ፪
አብረው በቀኙ ይቆማሉ ከሀዘን ይሰወራሉ፪
መኃሪ ጌታ ፈጣሪያችን ይድረስህ ልመናችን፪
በዚያ ግሩም ቀን እባክህን አቁመን በቀኝህ፪
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል በክበሩ ይገለጻል፪
አብረው ከእርሱ ጋር ይመጣሉ ቅዱሳን መላእክት ሁሉ፪
ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል በዙፋን ይቀመጣል፪
የምሕረት አዋጅ ይታወጃል ነፍስ ሁሉ ይጨነቃል፪
ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ በግራው ይቆማሉ፪
ቅዱስ ቃሉን ሰምተው ያመኑ የጸኑ በኪዳኑ፪
አብረው በቀኙ ይቆማሉ ከሀዘን ይሰወራሉ፪
መኃሪ ጌታ ፈጣሪያችን ይድረስህ ልመናችን፪
በዚያ ግሩም ቀን እባክህን አቁመን በቀኝህ፪
✦