አንደበትን ስጠኝ ጌታዬ
✦
አዳኙ ስምህን ዘወትር ልጠራበት
ቅዱስ ኃያል ህያው ክብር የምልበት
ከሃጢያት የራቀ ሐኬት የሌለበት
ምስጋናህን ብቻ የምናገርበት፪
አንደበትን ስጠኝ ጌታዬ፬
ሕይወት የሆነውን ቃልህን ሰባኪ
ገናናነትህን ክብርህን ተራኪ
ለንስሃ ህይወት በጎችህን ጠሪ
እንደ ሐዋሪያት ፍቅርህን መስካሪ፪
ከከሃድያን ጋር የማይተባበር
ፆምና ጸሎትን የሚያዘወትር
ከጽድቅ ስራ ጋር መልካም ህብረት ያለው
በምድራዊ ምኞት የማይታለለው፪
ፈተና ሲገጥመኝ በመከራ ጊዜ
የሀዘን ጥላ ጋርዶን ሲከበን ትካዜ
ተመስገን የሚል በችግር በደስታ
ርቱዕ አንደበትን ፍጠርልን ጌታ፪
ቅዱስ ኃያል ህያው ክብር የምልበት
ከሃጢያት የራቀ ሐኬት የሌለበት
ምስጋናህን ብቻ የምናገርበት፪
አንደበትን ስጠኝ ጌታዬ፬
ሕይወት የሆነውን ቃልህን ሰባኪ
ገናናነትህን ክብርህን ተራኪ
ለንስሃ ህይወት በጎችህን ጠሪ
እንደ ሐዋሪያት ፍቅርህን መስካሪ፪
ከከሃድያን ጋር የማይተባበር
ፆምና ጸሎትን የሚያዘወትር
ከጽድቅ ስራ ጋር መልካም ህብረት ያለው
በምድራዊ ምኞት የማይታለለው፪
ፈተና ሲገጥመኝ በመከራ ጊዜ
የሀዘን ጥላ ጋርዶን ሲከበን ትካዜ
ተመስገን የሚል በችግር በደስታ
ርቱዕ አንደበትን ፍጠርልን ጌታ፪
✦