አንዲት ናት ቤተክርስቲያን
✦
አንዲት ናት ቤተክርስትያን አንዲት ናት፪
ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
አዲስ አይደለንም ለመከራ ጉዞ
የወደቀ አናውቅም መስቀል ተመርኩዞ
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ነውና
በርቱ ክርስቲያኖች በእውነት ጎዳና፪
የአበውን እምነት በዐላውያን ፊት
ሰምተን ስላደግን ከገድላት አንደበት
መስዋእትነትም ቀርቧል ከፊታችን
እውነት ስትገፋ አይችልም ልባችን፪
አልጠፋችምና በእሳት ተፈትና
ይህን እናውቃለን በገሃድ ነውና
መሰደድ መቃጠል ሁሉም ለጊዜው ነው
ለእውነት ከሆነ ሞትም ክብራችን ነው፪
ከተዋሕዶ ጋር ስላለ መንፈሱ
እውነትን ለማጥፋት መቅደስ አታፍርሱ
በግፍ ቢገደሉ ክርስቲያኖች ሁሉ
ኦርቶዶክስ አጠፋም ተነግሯል በቃሉ
ተዋሕዶ አጠፋም ተነግሯል በቃሉ
ታሪክን ያኖረች ፊደላትን ቀርጻ
ቅርስን ያወረሰች ገዳማት አንፃ
እንግዳ ተቀባይ መንፈሳዊት እናት
ይህንን አትዘንጉ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት
ይህንን አትዘንጉ ተዋሕዶ ሀገር ናት::
+++
ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
አዲስ አይደለንም ለመከራ ጉዞ
የወደቀ አናውቅም መስቀል ተመርኩዞ
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ነውና
በርቱ ክርስቲያኖች በእውነት ጎዳና፪
የአበውን እምነት በዐላውያን ፊት
ሰምተን ስላደግን ከገድላት አንደበት
መስዋእትነትም ቀርቧል ከፊታችን
እውነት ስትገፋ አይችልም ልባችን፪
አልጠፋችምና በእሳት ተፈትና
ይህን እናውቃለን በገሃድ ነውና
መሰደድ መቃጠል ሁሉም ለጊዜው ነው
ለእውነት ከሆነ ሞትም ክብራችን ነው፪
ከተዋሕዶ ጋር ስላለ መንፈሱ
እውነትን ለማጥፋት መቅደስ አታፍርሱ
በግፍ ቢገደሉ ክርስቲያኖች ሁሉ
ኦርቶዶክስ አጠፋም ተነግሯል በቃሉ
ተዋሕዶ አጠፋም ተነግሯል በቃሉ
ታሪክን ያኖረች ፊደላትን ቀርጻ
ቅርስን ያወረሰች ገዳማት አንፃ
እንግዳ ተቀባይ መንፈሳዊት እናት
ይህንን አትዘንጉ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት
ይህንን አትዘንጉ ተዋሕዶ ሀገር ናት::
+++
✦