አንቀጸ ብርሃን
✦
አንቀፀ ብርሃን ድንግል ማርያም
ሰማያዊ ዙፋን የመድኃኔዓለም፪
ሰማይና ምድር የማይችሉትን
ኸረ እንደምን ቻልሽው ፍህም መለኮትን፪
የእሳት መጋረጃ ወዴት ተጋረደ
ልኡል በጥበቡ ካንቺ ተዋሐደ፪
የኪሩቤል አምሳል እመብርሃን ናት
ሰማያዊ ንጉሥ የከተመባት
የመለኮት ዙፋን ድንግል በመሆን
ሚካኤል ገብርኤል ሰግደው ዘመሩልሽ
ሩፋኤል ራጉኤል ሰግደው ዘመሩልሽ
ሰማያዊ ዙፋን የመድኃኔዓለም፪
ሰማይና ምድር የማይችሉትን
ኸረ እንደምን ቻልሽው ፍህም መለኮትን፪
የእሳት መጋረጃ ወዴት ተጋረደ
ልኡል በጥበቡ ካንቺ ተዋሐደ፪
የኪሩቤል አምሳል እመብርሃን ናት
ሰማያዊ ንጉሥ የከተመባት
የመለኮት ዙፋን ድንግል በመሆን
ሚካኤል ገብርኤል ሰግደው ዘመሩልሽ
ሩፋኤል ራጉኤል ሰግደው ዘመሩልሽ
✦