አንጻኝ

አንጻኝ እጠበኝ ከኃጢአቴ
አንተ ነህና መድኃኒቴ
አንተ ነህና ረዳቴ አንጻኝ እጠበኝ ከኃጢአቴ
ላንተ ይገዛ ሰውነቴ
ይቅር ከእንግዲህ መዋተቴ
ፊትህን መልስ ራራልኝ
ልኑር ከአንተ ጋር እዘንልኝ
እንዳልመለስ ወደኀእላ
የኃጢአትን ፍሬ እንዳልበላ
ጠብቀኝ እንጂ በኃይልህ
እንዳልወድቅብህ ልጅህ
ኃጢአቴን አጥበህ አሣርፈኝ
አምላኬ አንተነህ ሌላም የለኝ
እኔነቴን ሳስብ አሳዘነኝ
ልኑር ከአንተጋር እዘንልኝ
← መዝሙር