አረሳት ኢትዮጵያን

አረሳት ኢትዮጵያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በሰማይ
የተሸጋገረ በጽድቅ አደባባይ
ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠር ከተማ
የኢቲሳው አባትየደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ህይወቱ
ፋናው እስከዛሬ ሲያበራ የኖረው
የእቲሳው አባ ፍስሐ ጽዮን ነው
እግዙሐርያ እናቱ ማህጸነ ቡሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
ዲያብሎስ እስከ አሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲገረፍ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያን አባት
ሜዳና ቆላውን በመስቀል ባረካት
ምንጭና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
ያባታችን መስቀል ጸሎት ስለነካው
የተራመደበት የረገጠው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርናቅጠሉ
← መዝሙር