አርማዬ ነሽ

አርማዬ ነሽ
ኪዳነምህረት የተለየውብሽ
ከሞት መዳፍ ከጠላቴ ያመለጥኩብሽ (2x)
በሰማይ የታየሽ ነሽ ቀስተደመና
በሕብረ ቀለማት አጊጤሻልና
ዳግም ላያጠፋን ያየንሽ ምልክት
ለአዳም ከእኔ ልጁ የሆንሺው ትምክህት
ኪዳነምህረት በኪዳንሽ
ፀናልኝ ልቤ በምልጃሽ (2x)
መጨነቅ መተከዝ መቅበዝበዜ ቀረ
ስምሽ ምሽግ ሆኖኝ ታሪኬን ቀየረ
ስለ እረፍተ ሚስጢር ዓለም ሁሉ ይስማኝ
መስክሬ ኖራለሁ ስላንቺ ቃል አለኝ
ኪዳነምህረት በኪዳንሽ
ፀናልኝ ልቤ በምልጃሽ
እንደንስር ክንፎች ሃይልን ተላብሼ
ልቀኝልሽ ድንግል በፍቅርሽ ታድሼ
ሐሩሩን ማምለጫ የምህረት ደመና
ወጀቡን ማለፊያ መርከቤ ነሽና
ኪዳነምህረት በኪዳንሽ
ፀናልኝ ልቤ በምልጃሽ
ሞቴን እያየሁት አልፏል ከኋላዬ
ቃልኪዳንሽ ከቦኝ ሰመረ ጉዞዬ
የተደበኩብሽ የእረፍቴ ከተማ
መቼም የማረሳሽ የድህነቴ አርማ
ኪዳነምህረት በኪዳንሽ
ፀናልኝ ልቤ በምልጃሽ
← መዝሙር