አታውኪኝ ነፍሴ

አታውኪኝ ነፍሴ አታስጨንቂኝ
በዓለም መድኃኒት በእግዚአብሔር ታመኚ
ዋልያ እንደሚናፍቅ ወደ ውኃ ምንጮች
አቤቱ ወደ አንተ ነፍሴ ናፈቀች
መቼ ተነሥቼ መቼ እደርሳለሁ
የአምላኬን ፊቱን መቼ አየዋለሁ
የሕይወትን ውኃ እያስታወሰች
ነፍሴ ወደሕያው አምላክ ተጠማች
አታውኪኝ ነፍሴ አታስጨንቂኝ
በዓለም መድኃኒት በእግዚአብሔር ታመኚ
← መዝሙር