አትድፈር የማይደፈር
✦
እሳቱ ሰባት እጥፍ ቢነድም
ላቆምክልን ምስል አንሰግድም
ፀንተን እንቆማለን ባያድነን እንኳ
ሀይማኖታችንን አትድፈር አትንካ
በባቢሎን ምድር ብትሰጠንም ስልጣን
አያባብለንም አምላክ እስኪያሳጣን
በማይሻር ዙፋን የንጉስ ለጆች ነን
ሰይፍና መከራ እሳት የማይገርመን
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ..................
ቃላችን አንድ ነው አይቀያየርም
የእስራኤልን አምላክ በፍፁም አንክድም
በእምነት ሽረነዋል አዋጅህ ከንቱ ነው
አቃጥለህ ብትገድለን ሞት ህይወታችን ነው
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ..........................
የመለከቱ ድምፅ እንቢልታ ሲሰማ
መሰንቆና ክራር ሲነሳ በገና
እሳትህን ፈርቶ ከለዳዊው ቢሰግድ
አንሰግድልህም አሥር እጥፍ ይንደድ
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ...................
አገልጋዩን የእሳት ነበልባል ያደርጋል
እባብና ጊንጡን ፍሙንም ይረግጣል
እኛ የምናመልከው የማይጠፋ እሳት ነው
የማንቃጠለው ከእርሱ ተወልደን ነው
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ................
ላቆምክልን ምስል አንሰግድም
ፀንተን እንቆማለን ባያድነን እንኳ
ሀይማኖታችንን አትድፈር አትንካ
በባቢሎን ምድር ብትሰጠንም ስልጣን
አያባብለንም አምላክ እስኪያሳጣን
በማይሻር ዙፋን የንጉስ ለጆች ነን
ሰይፍና መከራ እሳት የማይገርመን
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ..................
ቃላችን አንድ ነው አይቀያየርም
የእስራኤልን አምላክ በፍፁም አንክድም
በእምነት ሽረነዋል አዋጅህ ከንቱ ነው
አቃጥለህ ብትገድለን ሞት ህይወታችን ነው
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ..........................
የመለከቱ ድምፅ እንቢልታ ሲሰማ
መሰንቆና ክራር ሲነሳ በገና
እሳትህን ፈርቶ ከለዳዊው ቢሰግድ
አንሰግድልህም አሥር እጥፍ ይንደድ
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ...................
አገልጋዩን የእሳት ነበልባል ያደርጋል
እባብና ጊንጡን ፍሙንም ይረግጣል
እኛ የምናመልከው የማይጠፋ እሳት ነው
የማንቃጠለው ከእርሱ ተወልደን ነው
አትድፈር የማይደፈር አትንካ የማይነካ
አዝ................
ዘማሪ ዲ.ን መኩሪያ ጉግሳ፣ ለምለም ከበደ
✦