አየሁት በሕልሜ

አየሁት በሕልሜ (2x)
ሞት የተባለሁን ሥጋ ተሸክሜ2x
ሰማሁት በዝና (2x)
ቀጠሮ አክባሪ ነው ሞት አይቀርምና (2x)
ዓለምን ለማዳን የተሰቀለው
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው
ጌታችን ተሰቅሎ ቢያዩት መላእክት
በዝማሬ ፈንታ አለቀሱለት
ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤል ገረመው
አምላኩ እርቃኑን ተሰቅሎ ስላየው
ነፍሱን ለወዳጁ የሚሰጥ ቢገኝም
ለጠላት የሚሞት በጭራሽ አይኖርም
ጠላቶቹ ስንሆን ለኛ የሞተው
ክርስቶስ ልዩ ነው ወደርም የለው
እውርን ቢያበራ የሞተን ቢያስነሣ
በመመስገን ፈንገታ ሆነበት አበሳ
ሰማያዊው ዳኛ ሊፈረድበት
ተከሶ ቀረበ በጲላጦስ ፊት
ዐርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው
ሥጋና ደሙን ለእኛ የሰጠው
ፍቅር አስገድዶት ለኛ የሞተው
መልካሙ እረኛችን መድኃኔ ዓለም ነው
← መዝሙር