አዘክሪ ድንግል

አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
ካንቺ መወለዱን አዘክሪ
በቤተልሔም አዘክሪ
በጨርቅ መጠቅለሉን አዘክሪ
መኝው ግርግም አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በዚያ በብርድ ወራት አዘክሪ
የገበሩለትን አዘክሪ
የአድግና የላም አዘክሪ
እስትንፋሣቸውን አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በግብጽ በረሃ አዘክሪ
መሠደድሽን አዘክሪ
የአሸዋውን ግለት አዘክሪ
ርሃቡና ጥሙን $ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
በመቃብሩ ዘንድ አዘክሪ
ባነባሽው እንባ አዘክሪ
አሳስቢ ድንግል ሆይ አዘክሪ
ገነት እንድንገባ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
← መዝሙር