ባክኛለሁና

ባክኛለሁና በሥጋ ፈተና
የዚህ ዓለም ሐዘን ጫፍ የለውምና
ፈጥነሽ ወደ እኔ ነይ ከትንሻእ ቤቴ
አጽናኚኝ እመአምላክ ድንግል እመቤቴ
ባሕሩ ትልቅ ነው ድንግል እመቤቴ
ትንሽ ናት መርከቤ ድንግል እመቤቴ
የመንገዴ መሪ ድንግል እመቤቴ
አንቺ ነሽ ወደቤ ድንግል እመቤቴ
በመንገዴ ብዝል ድንግል እመቤቴ
ዓለም ትስቃለች ድንግል እመቤቴ
መመኪያ እመቤቱ ድንግል እመቤቴ
ወደየት ናት እያለች ድንግል እመቤቴ
በቀቢጸ ተስፋ ድንግል እመቤቴ
እንዳልወደልቅብሽ ድንግል እመቤቴ
በቀንም በሌሊት ድንግል እመቤቴ
ተስፋዬ አንቺ ነሽ ድንግል እመቤቴ
የለም ያተረፍኩት ድንግል እመቤቴ
ወጥቼ ወርጄ ድንግል እመቤቴ
ትርፌ አንቺ ብቻ ነሽ ድንግል እመቤቴ
ጽዮን አማላጄ ድንግል እመቤቴ
← መዝሙር