ባለውለታዬ

ባለውለታዬ ከአመድ ያነሳኸኝ
ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ
በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ
ዝቅ አድርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘ ጌታዬ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ
ባለውለታዬ ከአመድ ያነሳኸኝ
ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ሥራዬ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታዬ
ማዕረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ
ባለውለታዬ ከአመድ ያነሳኸኝ
ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ
ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ
ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ
ፈረደችባቸው ኃጢአትም በእነርሱ
በሰላም ሂጂ አለኝ ምሮኛል ንጉሡ
ባለውለታዬ ከአመድ ያነሳኸኝ
ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ
የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ
በሠራልኝ ሥራ በዕድሜ ዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ
← መዝሙር