ባሰማት ጊዜ

ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልኝም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና
ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ
ድንግል ቀረበች ወደ እርሱ ፍጹም ትኅትናን ይዛ
ትፀንሻለሽ ሲላት መልአኩ ፍጹም በልቧ ሳትመኝ
እንደ ቃልህ ይን አለችው በቃሉ ተማርኝ
አዝ . . .
ዓለም መድኃኒት ነውና ከአንቺ የሚወለደው መንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙንም ብለሽ ኢየሱስ
አዝ . . .
እጹብ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ለድንግል ማርያም የተሰጣት እድል
የአምላክ እናት ሆኖ መመረጥ ከሴቶች መኝከል
አዝ . . .
ጸጋን የተመላሽ ሆይ ይገባሻል ለአንቺ ክብርና ምስጋና
የክብር ባለቤት ሁል ጊዜም ከአንቺ ጋር ነውና
← መዝሙር