በአምስቱ አዕማድ
✦
በርትዕት ሃይማኖት እንዲጸና ልባችን
በኑፋቄ ማዕበል እንዳይናድ መሰረታችን
በአምስቱ አዕማድ ይታነጽ ቤታችን
በኑፋቄ ማዕበል እንዳይናድ መሰረታችን
በአምስቱ አዕማድ ይታነጽ ቤታችን
ምስጢረ ሥላሴ አንድነት ሦስትነት
አንድ አገዛዝ ባሕርይ ሦስት ስም አካላት
በሦስቱ ኩነታት ልብ ቃል እስትንፋስ
አንድ አምላክ ነውና ደግሞም ሥሉስ ቅዱስ
አዝ
አንድ አገዛዝ ባሕርይ ሦስት ስም አካላት
በሦስቱ ኩነታት ልብ ቃል እስትንፋስ
አንድ አምላክ ነውና ደግሞም ሥሉስ ቅዱስ
አዝ
ከሦስቱ አካላት ወልድ አካላዊ ቃል
ያለ የነበረ ኢየሱስ ክርስቶስ
ያለዘርዐ ብእሲ ከድንግል ማርያም
ተወልዶ አየነው እጹብ ድንቅ እንበል
አዝ
ያለ የነበረ ኢየሱስ ክርስቶስ
ያለዘርዐ ብእሲ ከድንግል ማርያም
ተወልዶ አየነው እጹብ ድንቅ እንበል
አዝ
በሠላሳ ዓመቱ በዕደ ዮሐንስ
ተጠምቆ አየነው በማየ ዮርዳኖስ
ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም እንድንወለድ
ይገባል መጠመቅ ልጆቹ እንድንሆን
አዝ
ተጠምቆ አየነው በማየ ዮርዳኖስ
ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም እንድንወለድ
ይገባል መጠመቅ ልጆቹ እንድንሆን
አዝ
ከገነት ብንወጣ ከመንግስቱ ርቀን
ሲዖል ብንገባም ለኃጢአት ተሽጠን
ገነት እንድንገባ ታረቀን መልሶ
ቅዱስ አማኑኤል ሥጋ ደሙን ክሶ
አዝ
ሲዖል ብንገባም ለኃጢአት ተሽጠን
ገነት እንድንገባ ታረቀን መልሶ
ቅዱስ አማኑኤል ሥጋ ደሙን ክሶ
አዝ
ሞተን እንደማንቀር አረጋገጠልን
በቅድስት ትንሣኤው ሞትን ገደለልን
ክርስቶስ ሲገለጥ በዳግም ምጽአቱ
ጻድቁም ኃጥኡም ይቆማል ከፊቱ
በቅድስት ትንሣኤው ሞትን ገደለልን
ክርስቶስ ሲገለጥ በዳግም ምጽአቱ
ጻድቁም ኃጥኡም ይቆማል ከፊቱ
✦