በበረት የተኛው
✦
በበረት የተኛው ቅዱሱ ሕፃን
ልብስም አለበሰ ነበረ እርቃኑን
የምታለብሰው ልብስ ባታገኝ እናቱ
ትንፋሽ አለበሱት ከበው እንስሳቱ
እሰይ የምሥራች ሃሌ ሃሌ ሉያ
ጌታ ተወለደ ሊሆነን አርዓያ
ልብስም አለበሰ ነበረ እርቃኑን
የምታለብሰው ልብስ ባታገኝ እናቱ
ትንፋሽ አለበሱት ከበው እንስሳቱ
እሰይ የምሥራች ሃሌ ሃሌ ሉያ
ጌታ ተወለደ ሊሆነን አርዓያ
✦