በእምነታቸው ዳኑ
✦
በእምነታቸው ዳኑ ከዚያ ነበልባል፪
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል፪
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል፪
ናቡከደነፆር ጨካኙ ንጉሥ
በባቢሎን ሀገር ጣዖት የሚያነግሥ
እያለ ስገዱ አማኙን ሲያምስ
ወጣቶች ተነሡ በቅናት መንፈስ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል፪
በባቢሎን ሀገር ጣዖት የሚያነግሥ
እያለ ስገዱ አማኙን ሲያምስ
ወጣቶች ተነሡ በቅናት መንፈስ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል፪
ለሠራኸው ጣዖት አንሰግድም እያሉ
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልባቸውን ሞሉ
የፈጠረን አምላክ ያድናል ሲሉ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ፪
አዘ ------------
ነበልባል ነዲዱ እንዲያቃጥላቸው
በጭካኔ መንፈስ አስወረወራቸው
ገብተው ሲጸልዩ ፍህሙ ሳይነካቸው
መልአኩን ልኮ አበረደላቸው
ገብርኤል ፪ በመስቀል ፪
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልባቸውን ሞሉ
የፈጠረን አምላክ ያድናል ሲሉ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ፪
አዘ ------------
ነበልባል ነዲዱ እንዲያቃጥላቸው
በጭካኔ መንፈስ አስወረወራቸው
ገብተው ሲጸልዩ ፍህሙ ሳይነካቸው
መልአኩን ልኮ አበረደላቸው
ገብርኤል ፪ በመስቀል ፪
እንደ ሦስቱ ሕፃናት በእምነት ለሚቆመው
መልአኩን ይልካል እግዚአብሔር ሊረዳው
እሳቱም ይበርዳል መልአኩን ሲልከው
ገብርኤል ፪በመስቀል
መልአኩን ይልካል እግዚአብሔር ሊረዳው
እሳቱም ይበርዳል መልአኩን ሲልከው
ገብርኤል ፪በመስቀል
በእምነታቸው ዳኑ ከዚያ ነበልባል፪
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል፪
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል፪
✦