በእፀ መስቀሉ

በእፀ መስቀሉ የተከፈለልኝ
የኢየሱስ ፍቅር ምንኛ ማረከኝ
ከፍቅርም በላይ ሆነና መሰጠኝ
ከመስቀል ስር ሆኘ ፊቱን እያየሁኝ
አዝ======
አለምን በፍቅሩ ያሸነፈ ጌታ
የፀብን ማእበል በፍቅሩ የገታ
ህይወቴን ፀጥ አድርጎ ይምራ በብልሀቱ
እኔ ምን አለፋኝ አልደክምም በከንቱ
አዝ======
ደሙ ከወዙ ጋር ተዋህዶ ሲወርድ
በኔ በደል ጌታየ ቀረበልኝ ለፍርድ
ሀጥያቴን በጫንቃዉ ተሸክሞልኛል
በደሌን ደምስሶ ንፁህ አድርጎኛል
አዝ========
የቀራንዮ ግፍ ባንተ ላይ የሆነዉ
ሰይጣንን ጠርቆ ከመንገድ አወጣዉ
እሾህ አሜኬላዉ ተደምስሶልናል
የንፁሁ በግ ደም አዳምን ታድጉአል
አዝ=========
ይህንን ስጋየን ብሉ ይላችሁአል
ይህንን ደሜንም ጠጡ ይላችሁአል
ከመስቀል ስር ሆነን ደሙን እንቀበል
ስጋዉን እንብላ ሰዎች ችላ አንበል
በእፀ መስቀሉ የተከፈለልኝ
የኢየሱስ ፍቅር ምንኛ ማረከኝ
ከፍቅርም በላይ ሆነና መሰጠኝ
ከመስቀል ስር ሆኘ ፊቱን እያየሁኝ
← መዝሙር