በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል
✦
በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል
ድርሻ የተሰጠህ ሰውን ለማገልገል
ተራዳኢ መልአክ ጠባቂ የእስራኤል
የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል
ድርሻ የተሰጠህ ሰውን ለማገልገል
ተራዳኢ መልአክ ጠባቂ የእስራኤል
የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል
አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
ፈረዖን በእስራኤል ላይ በትዕቢት ተነሥቶ
ቢከታተላቸው ጦሩን አስነሥቶ
ይመራቸው ጀመር ሚካኤል በፋና
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
ቢከታተላቸው ጦሩን አስነሥቶ
ይመራቸው ጀመር ሚካኤል በፋና
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
ከባህር ያወጣኸው ጸጋ ዘአብን
ከአረመኔው ንጉስ እግዚእ ሐሪያን
ከልለህ የጠበቅህ በብዙ ተዓምራት
እኛንም ጠብቀን ከበደል ከሃጢያት
ከአረመኔው ንጉስ እግዚእ ሐሪያን
ከልለህ የጠበቅህ በብዙ ተዓምራት
እኛንም ጠብቀን ከበደል ከሃጢያት
አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
በአፎሚያ ላይ ሲፎክር ጠላት
ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላዕክት
እኛንም ጠብቀን ከክፉ ከቅሰፍት
ፈጥነህ ድረስልን ሁነን ረዳት
ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላዕክት
እኛንም ጠብቀን ከክፉ ከቅሰፍት
ፈጥነህ ድረስልን ሁነን ረዳት
አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
መልአኩ ሚካኤል አማላጃችን
እንለምንሃለን እንድትጠብቀን
አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ
ዋስ ጠበቃ ሁነን ሚካኤል አደራ
እንለምንሃለን እንድትጠብቀን
አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ
ዋስ ጠበቃ ሁነን ሚካኤል አደራ
✦