በገና አንሥተን

በገና አንሥተን መሰንቆን
እናመስግነው ስምህን
አንደ አምላካቸን ማንም የለም
ይክበር ይመስገን ለዘለዓለም
ዓለም ሞኝነት ይመስለዋል
ለአንተ መንበርከክ ይከብደዋል
ፍቅርህን ቀምሰን ዝም አንልም
እንዘምራለን ለዘለዓለም
ሞኝነት ለእኔ መች ሆነና
ፊትህ ያቆመኝ ለምስጋና
እንድቀኝልህ ግድ የሚለኝ
ፍቅርህ ብቻ ነው የማረከኝ
ፈውስን ስትሰጠን ስትባርከን
ፍቅርህን ልከህ ስትጎበኘን
ጉልበት ይጸናል በአንተ ጸጋ
ማነው የሚከፍልህ የአንተን ዋጋ
ስንዘምርልህ የሚስቁ
ብዙ ሜልኮሎች ዛሬም አሉ
የእኛ የሆነ ምንም የለም
አምላክ ስላንተ ዝም አንልም
← መዝሙር