በጌቴ ሰማኔ

በጌቴ ሰማኔ በአታክልቱ ቦታ
ለእኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ
አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት
እኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት
መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ
ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ
በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው
እንዲህ ሲል ጸለዬ አባት ሆይ ማራቸው
በረቂቅ ስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ
በረቂቅ ጥበቡ ሁሉን የፈጠረ
በሰው እጅ ተገርፎ ሞተ ተቀበረ
← መዝሙር