በጌቴ ሴማኔ

በጌቴ ሴማኔ በአትክልቱ ቦታ
ለኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ
አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት
እኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት
ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ
መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ
በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው
እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ሆይ ማራቸው
ተጠማሁ፣ተጠማሁ፣ተጠማሁ፣ ሲላቸው
ሆምጣጤ አመጡለት በሰፍነጉ ሞልተው
በረቂቅ ጥበቡ ሁሉን የፈጠረ
በሰዎች ተገርፎ ሞቶ ተቀበረ
ዘማሪ ሢራክ ታደሰ
← መዝሙር