በሐዘኔ ደራሽ ነሽ በጭንቀቴ

በሐዘኔ ደራሽ ነሽ በጭንቀቴ
በችግሬም ደራሽ ነሽ
የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት
ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል
መልካሚቷ እርግብ ድንግል እመቤቴ
ማርያም እናቴ ነሽ
ከፍጥረታት ሁሉ
ገናና ነው ክብርሽ
የሐዘኔ መጽናኛ
ዕንባዬን አባሽ ነሽ
ዋሻ መጠለያ ድንግል እመቤቴ
የዘላለም ቤቴ
መንገድ ስሄድ ስንቄ
መጠጤ ነሽ ምግቤ
እመ አምላክ ስጠራሽ
ይጠፋል እረሃቤ
የእናትነሽን አየሁት ድንግል እመቤቴ
ፍቅርሽን አየሁት
ጎጆዬን ስትሞይው
ባዶ የሆነውን
አንቺ እያለሽልኝ
ምን እሆናለሁኝ
← መዝሙር