በኀዘኔ

በኀዘኔ ደራሽ ነሽ በጭንቀቴ
በችግሬ ደራሽ ነሽ
የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት
ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል /፪
መላካሚቱ ርግብ ድንግል እመቤቴ
ማርያም እናቴነሽ ድንግል እመቤቴ
ከፍጥረታት ሁሉ ድንግል እመቤቴ
ገናና ነው ክብርሽ ድንግል እመቤቴ
በኀዘኔ መጽናኛ ድንግል እመቤቴ
እንባዬን አባሽ ነሽ ድንግል እመቤቴ
አዝ ---------
ዋሻ መጠለያ ድንግል እመቤቴ
የዘለዓለም ቤቴ ድንግል እመቤቴ
መንገድ ስሄድ ስንቄ ድንግል እመቤቴ
መጠጤ ነሽ ምግቤ ድንግል እመቤቴ
እመአምላክ ስጠራሽ ድንግል እመቤቴ
ይጠፋል ረሀቤ ድንግል እመቤቴ
አዝ ------------
የእናትነትሽ ድንግል እመቤቴ
ፍቅርሽን አየሁት ድንግል እመቤቴ
ጎጆዬን ስትሞይው ድንግል እመቤቴ
ባዶ የሆነውን ድንግል እመቤቴ
አንቺ እያለሽልኝ ድንግል እመቤቴ
ምን እሆናለሁኝ ድንግል እመቤቴ
አዝ ------------
← መዝሙር