በኢያሪኮ መንገድ
✦
በኢያሪኮ መንገድ ጌታ አንተ ስታልፍ
ግፊያ ሆኖ ስደነቃቀፍ
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ተማጸንኩህ
ዓይኔንም ፈወስከኝ ዛሬ ማየት ቻልኩኝ፪
አንተን እንዳላይ ቁመቴ አጠረብኝ
ከፊት እየሮጥኩ ከዛፍ ላይ ወጣሁኝ
ጌታ ሆይ ጠረኸኝ ዘኬዎስ ሆይ አልከኝ
ቤቴ እንድትገባ ፍቃድህ ሆነልኝ፪
ሐሴትም ሆነልኝ በጣምም ደስ አለኝ
አንተን በእንግድነት በቤቴ ተቀበልኩኝ
ኃጢአቴን ሁሉ በአንተ ፊት ጥያለሁ
ሀብቴን አካፍል ዘንድ እንዲገባ አውቃለሁ፪
የክፋትን ገንዘብ መስብሰቤን ትቼ
አንተን ልክተልህ ሁሉን ረስቼ
ኑሮዬንም ባርከው የሕይወት ዘመኔን
መርጫለሁ አንተን በቤትህ መኖሬን፪
ግፊያ ሆኖ ስደነቃቀፍ
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ተማጸንኩህ
ዓይኔንም ፈወስከኝ ዛሬ ማየት ቻልኩኝ፪
አንተን እንዳላይ ቁመቴ አጠረብኝ
ከፊት እየሮጥኩ ከዛፍ ላይ ወጣሁኝ
ጌታ ሆይ ጠረኸኝ ዘኬዎስ ሆይ አልከኝ
ቤቴ እንድትገባ ፍቃድህ ሆነልኝ፪
ሐሴትም ሆነልኝ በጣምም ደስ አለኝ
አንተን በእንግድነት በቤቴ ተቀበልኩኝ
ኃጢአቴን ሁሉ በአንተ ፊት ጥያለሁ
ሀብቴን አካፍል ዘንድ እንዲገባ አውቃለሁ፪
የክፋትን ገንዘብ መስብሰቤን ትቼ
አንተን ልክተልህ ሁሉን ረስቼ
ኑሮዬንም ባርከው የሕይወት ዘመኔን
መርጫለሁ አንተን በቤትህ መኖሬን፪
✦