በክብር ዙፋኑ
✦
በክብር ዙፋኑ መርጦ ያስቀመጠሽ
ለእኛ ለኃጢአተኞች ተስፋችን አንቺው ነሽ
በፍጹም ንጽሕና ቤተመቅደስ ያደግሽ
የአማኑኤል የጌታዬ የፈጣሪ እናት በምን እንመስልሽ፪
ቃና ዘገሊላ ሠርግ ደግሰው
አንቺን ከነልጅሽ በክብር ጠርተው
ሰዎች ተረብሸው በጣም ተደናግጠው
ወይኑ በማለቁ በፍርሃት ተውጠው
ለእኛ ለኃጢአተኞች ተስፋችን አንቺው ነሽ
በፍጹም ንጽሕና ቤተመቅደስ ያደግሽ
የአማኑኤል የጌታዬ የፈጣሪ እናት በምን እንመስልሽ፪
ቃና ዘገሊላ ሠርግ ደግሰው
አንቺን ከነልጅሽ በክብር ጠርተው
ሰዎች ተረብሸው በጣም ተደናግጠው
ወይኑ በማለቁ በፍርሃት ተውጠው
አዝ ---
ወይኑ በመሃል ላይ ማለቁን ሰምተሽ
ድንጋጤአቸውን እመበቴ አይተሽ
ወደ ልጅሸ ሄደሽ ብትጠይቂላቸው
ጋኑን ውኃ ሙሉት ብሎ አዘዛቸው
አዝ ---
ውኃውን ወደወይን አጣፍጦ ቀይሮ
የዶኪማስንም እፍረቱን ሰውሮ
እድምተኞች ሁሉ እስከሚደነቁ
አምላክ ከእነእርሱ ጋር መሆኑን አወቁ
አዝ ---
ወይኑ በመሃል ላይ ማለቁን ሰምተሽ
ድንጋጤአቸውን እመበቴ አይተሽ
ወደ ልጅሸ ሄደሽ ብትጠይቂላቸው
ጋኑን ውኃ ሙሉት ብሎ አዘዛቸው
አዝ ---
ውኃውን ወደወይን አጣፍጦ ቀይሮ
የዶኪማስንም እፍረቱን ሰውሮ
እድምተኞች ሁሉ እስከሚደነቁ
አምላክ ከእነእርሱ ጋር መሆኑን አወቁ
አዝ ---
✦