በከሃሊነቱ
✦
በከሃሊነቱ በአምላክነቱ ፪
ይቅር ይለናል ይታደገናል፪ በቸርነቱ
ምን ይከፈለዋል ምን ይሆን ዋጋው
ለፈጠረን ጌታ ለይቅር ባዩ
የድኅነትን መንገድ ንስሓን የሠራ
እንዳንጠፋበት ነው ዳግም በመከራ
ይቅር ይለናል ይታደገናል፪ በቸርነቱ
የሰው ልጅ ከኃጢአት እስኪመለሰ ድረስ
አይቸኩልም እርሱ መዓትን ለማድረስ
ትእግሥቱ ሰፊ ነው ሥራው እረቂቅ
ቸርነት ገንዘቡ ቢሰጠው አልያቅ
ይቅር ይለናል ይታደገናል፪ በቸርነቱ
ይቅር ይለናል ይታደገናል፪ በቸርነቱ
ምን ይከፈለዋል ምን ይሆን ዋጋው
ለፈጠረን ጌታ ለይቅር ባዩ
የድኅነትን መንገድ ንስሓን የሠራ
እንዳንጠፋበት ነው ዳግም በመከራ
ይቅር ይለናል ይታደገናል፪ በቸርነቱ
የሰው ልጅ ከኃጢአት እስኪመለሰ ድረስ
አይቸኩልም እርሱ መዓትን ለማድረስ
ትእግሥቱ ሰፊ ነው ሥራው እረቂቅ
ቸርነት ገንዘቡ ቢሰጠው አልያቅ
ይቅር ይለናል ይታደገናል፪ በቸርነቱ
✦