በልዑል መጠጊያ

በልኡል መጠጊያ የሚኖር በልኡል መጠጊያ
ይከልላል ከክፉ
አንደበቱን ከኃጢአት ከልክሎ አምላኩን ካሰበ
ካልተመጻደቀ በሥራው ራሱን ካልካበ
ይከለላል ከክፉ
ጨርቄን ማቄን ሳይል ራሱን ለአምላኩ ከሰጠ
በዓለም ምደራዊ ሀብት ተታሎ አምላኩን ካልሸጠ
ይከለላል ከክፉ
እስከመጨረሻው ለመኖር በእምነቱ ከጸና
ካላፈገፈገ ከአምላኩ ሲገጥመው ፈተና
ይከለላል ከክፉ
← መዝሙር