በማህፀን ቅኔ
✦
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች
ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች
በሀሴት ዘመረ ዘለለ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
በደንግል ማህፀን ስላየ ማዳኑን
ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን
ትንቢቱ ሲፈፀም በሆዷ ሲነግስ
ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ
ተፈጥሮ መች ቻለች ነብዩን ለማገድ
አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና
በእናቱ ማህፀን ድምፅን አሰማና
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ ገረማት
ልጇ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝላት
ድምጿን ከፍ አረገች አለም እንዲሰማ
ሞላት መንፈስ ቅዱስ በመዝሙር በዜማ
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች
ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች
በሀሴት ዘመረ ዘለለ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
በደንግል ማህፀን ስላየ ማዳኑን
ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን
ትንቢቱ ሲፈፀም በሆዷ ሲነግስ
ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ
ተፈጥሮ መች ቻለች ነብዩን ለማገድ
አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና
በእናቱ ማህፀን ድምፅን አሰማና
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ ገረማት
ልጇ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝላት
ድምጿን ከፍ አረገች አለም እንዲሰማ
ሞላት መንፈስ ቅዱስ በመዝሙር በዜማ
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው አገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሐ ያደገው
ድንግል ሰትናገር ምን እንዳዘለለው
✦