በማየ ቃና

እመቤታችን ባንቺ ምልጃ
ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና
ለጌታችን ተአምር----በማየ ቃና
ተመርጣ ታድላ---በማየ ቃና
መጀመሪያ ሆነች-----በማየ ቃና
ቃና ዘገሊላ----በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ
እመቤታችን ባንቺ ምልጃ
ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና
ታውቋት ስላለችው----በማየ ቃና
ወይንኬ አልቦሙ----በማየ ቃና
ውኃ ወይን ሲሆን----በማየ ቃና
ሁሉ አዩ ሰሙ----በማየ ቃና
ቃናን ሊያዳርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ
እመቤታችን ባንቺ ምልጃ
ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና
አሳላፊዎቹ----በማየ ቃና
ግራ ቢገባቸው----በማየ ቃና
የድንግል ማርያም ልጅ----በማየ ቃና
ከጭንቅ አወጣቸው----በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ
እመቤታችን ባንቺ ምልጃ
ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና
እኛም እናምናለን----በማየ ቃና
ተስፋ ትንብልና----በማየ ቃና
ስለ ቃልኪዳኗ----በማየ ቃና
ሁሉ እንደሚቃና----በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ ይምልጃ ሥራ
እመቤታችን ባንቺ ምልጃ
ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና
← መዝሙር