በመጨረሻው እንነሳለን ከሙታን

በመጨረሻው እንነሳለን ከሙታን
ጌታ ሲመጣ በአየር ሆነን እያየን
ብርሃን ሆኖ ለሚኖሩት ይህ ክብር
የሚናፈቅ ነው በልቦናቸው የሚኖር
የስንዴ ቅንጣት ትንሳኤካላት በምድር
ተስፋ አለን እኛ በሰማይ አገር ልንኖር
#አዝ
ፀሐይ ሲጨልም ክዋክብትም ሲረግፉ
ምድርና ሞላዋ ለዘላለም ሲያልፉ
በሰማይ ኃይላት ንውፅውፅታ ሲሰማ
ጌታ ይመጣል በመለኮቱ ግርማ
#አዝ
እልፍአእላፋት መላእክትም ሲታዩ
ብርሃን ሲሞላ ምድርና ሰማዩ
የምድር ዳረቻ በነፋሳት ኃይል ሲመታ
ከጭንቅ አድነን አማኑኤል የኛ ጌታ
#አዝ
ለሚታመኑ በሃይማኖት ለፀኑ
ይታያል በግልፅ የጌታችን ማዳኑ
በምድር እያሉ ኃጢያትን ለሚሰሩ
ያስደንግጣል ያስፈራቸዋል ክብሩ
#አዝ
ጌታ በዚያ ቀን እንዳንጣል ሲኦል
ቅዱስ ስምህን ይዘናል ተማፅነናል
በበደላችን እንዳትከፍለን አደራ
← መዝሙር