በሞት ጥላ ወድቀን

በሞት ጥላ ወድቀን ስንከራተት
በረቀቀው ፍቅሩ ዋጀን ከጥፋት
በጎልጎታ የታይ ፍጹም መድኃኒት
ሃሌ ሃሌ ሉያ ለአንድ ለኃያሉ ጌታ
ስለእኛ ተዋረድክ በጎልጎታ
የሞት ሸክም ከብዶን በጣር ስንባዝን
ወረደ ከሰማይ መጣ ሊያድነን
ከባርነት ቀንበር ነጻ ሊያወጣን
አዝ ---
ምንም ባልበደለ ምንም ባላጠፋው
ሁሉን ማድረግ ሲቻል ደካማ የሆነው
ሕይወትን ሊድለን ስለወደደን ነው
አዝ ---
እስቲ አስትውሉ የፍቅሩን ብዛት
ለመስቀሉ ሞት ታዝዞ እኛን ያዳነበት
ምንም አቻ የለው የጌታ ቸርነት
አዝ ---
← መዝሙር