በንፁህ ደሙ ያዳነን
✦
በንፁህ ደሙ ያዳነን
ከወደቅንበት ያነሳን
ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዘምራለን ለጌታ
ቀና ብለናል በክብር
አንገቱን ደፍቶ በፍቅር
ስለእኛ ብዙ ሆኖልን
የብርሃን አክሊል ደፋልን
የአለም መድሐኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው
እርቃኑን ሆኖ ሸለመን
እየደከመ አቆመን
እርሱ በመስቀል ሲሞት
እኛ ተጻፍን በህይወት
እስከ ሺህ ትውልድ ይምራል
ፍቅር ነውና ይራራል
አይዝልም የእርሱ ትከሻ
መጨረሻ ነው መድረሻ
በደም ያጌጠ ልብስ አለው
ከአማልክት ማንም አይመስለው
ትውልዱ ማዳኑን ይስማ
ነግሷል በጽዮን ከተማ
ከወደቅንበት ያነሳን
ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዘምራለን ለጌታ
ቀና ብለናል በክብር
አንገቱን ደፍቶ በፍቅር
ስለእኛ ብዙ ሆኖልን
የብርሃን አክሊል ደፋልን
የአለም መድሐኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው
እርቃኑን ሆኖ ሸለመን
እየደከመ አቆመን
እርሱ በመስቀል ሲሞት
እኛ ተጻፍን በህይወት
እስከ ሺህ ትውልድ ይምራል
ፍቅር ነውና ይራራል
አይዝልም የእርሱ ትከሻ
መጨረሻ ነው መድረሻ
በደም ያጌጠ ልብስ አለው
ከአማልክት ማንም አይመስለው
ትውልዱ ማዳኑን ይስማ
ነግሷል በጽዮን ከተማ
✦