በረቀቀው ፍቅርህ

በረቀቀው ፍቅርህ አንተ ብትጠራኝ ዛሬ
ይኸው ዳግመኛ መጣሁ በኃጢአት ዓለም ኖሬ
ከቤትህ እርቄ ብሄድ ለዓለም ተገዛሁ
አንተ ይቅር ትለኝ ዘንድ እንደገና መጣሁ
በቆረስከው ሥጋህ ባፈሰስከው ደምህ
ከዓለም ግዞት አውጥተህ አኑረኝ በቤትህ
ዳግመኛ እንዳልበድልህ በዓለም ተታልየ
በቅዱሳንህ ምልጃ ጠብቀኝ ጌታየ
በዓለም የሰራሁትን ያሳዘንሁህን ሁሉ
ይቅር በለኝ አምላኬ ስለ እግዝእትነ ኩሉ
በረቀቀው ፍቅርህ አንተ ብትጠራኝ ዛሬ
ይኸው ዳግመኛ መጣሁ በኃጢአት ዓለም ኖሬ
← መዝሙር