በሠርጋችን ዕለት
✦
በሠርጋችን እለት እንድትባርከን
ጌታ ጠርተንሃል በእምነት ሆነን
ከእናትህ ጋራ ከእመቤታችን
ከመላእክትህ ጋር ና በሠርጋችን
ከሐዋርያት ጋር ና በሠርጋችን
ከወዳጆችህ ጋር ና በሠርጋችን
በገሊላ መንደር እንደተገኘህ
ና በእኛ ድንኳንም ጌታ ሰንጠራህ
የጥሪ ወረቀት ልከናል እንዳትቀር
አንተነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር
ነይ ከልጅሽ ጋራ እመቤታችን
እንድታሟይልን የጎደለውን
ንገሪው ለልጅሽ ባዶው እንዲሞላ
በረከት የእርሱ ነው ቤታችንን ይሙላ
አዝ ---
በጐደለው ሁሉ እየጨመርሸልን
ቤታችንን ሁሉ ሙይው እናታችን
ለአገልጋዬቹም ድንግል ንግሪአቸው
ጠርተን እንዳናፍር ጋኖቹን ይሙላቸው
አዝ ---
ጌታ ጠርተንሃል በእምነት ሆነን
ከእናትህ ጋራ ከእመቤታችን
ከመላእክትህ ጋር ና በሠርጋችን
ከሐዋርያት ጋር ና በሠርጋችን
ከወዳጆችህ ጋር ና በሠርጋችን
በገሊላ መንደር እንደተገኘህ
ና በእኛ ድንኳንም ጌታ ሰንጠራህ
የጥሪ ወረቀት ልከናል እንዳትቀር
አንተነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር
ነይ ከልጅሽ ጋራ እመቤታችን
እንድታሟይልን የጎደለውን
ንገሪው ለልጅሽ ባዶው እንዲሞላ
በረከት የእርሱ ነው ቤታችንን ይሙላ
አዝ ---
በጐደለው ሁሉ እየጨመርሸልን
ቤታችንን ሁሉ ሙይው እናታችን
ለአገልጋዬቹም ድንግል ንግሪአቸው
ጠርተን እንዳናፍር ጋኖቹን ይሙላቸው
አዝ ---
✦