በሥራዮ የት ይሆን

በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ
ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍሴ ወዲያልኝ
ተሸክሜ የኃጥያት ክምር
ይመሻል ይነጋል በከንቱ ስዞር
ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ /2
በድያለሁ ወደ አንተ እጮሃለሁ
ይቅር በለኝ እማጸንሃለሁ
ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜአለሁ
አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ
እየጓጓሁ ለዚች ለሥጋዬ
በንስሓ ሳላጥበው እድፌን
ልትደርሰ ነው ያች የፈተና ቀን
← መዝሙር