ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
✦
ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መሥርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
አዝማች.......
ሁሉንም በሁሉ በሚሞላው ጌታ
ሙሽራው የሆነ ቤቱ ተሰኝታ
በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ
ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ፪
አዝማች.......
ዲያቢሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ
ወጥመድ ቢዘረጋ በጉዟችን ሁሉ
እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን
አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን፪
አዝማች.......
በስሙ መሰብሰብ በስሙ መሥራት
ስለ ስሙ መኖር ለስሙ መሞት
ጠላት ዲያቢሎስን ምን ባያስደስትም
ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ሕይወት፪
አዝማች.......
ከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው
ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው
አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት
ሃይማኖታችን ነው የኛ እርስት ጉልት፪
የሰጠንን አምላክ በደሙ መሥርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
አዝማች.......
ሁሉንም በሁሉ በሚሞላው ጌታ
ሙሽራው የሆነ ቤቱ ተሰኝታ
በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ
ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ፪
አዝማች.......
ዲያቢሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ
ወጥመድ ቢዘረጋ በጉዟችን ሁሉ
እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን
አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን፪
አዝማች.......
በስሙ መሰብሰብ በስሙ መሥራት
ስለ ስሙ መኖር ለስሙ መሞት
ጠላት ዲያቢሎስን ምን ባያስደስትም
ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ሕይወት፪
አዝማች.......
ከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው
ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው
አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት
ሃይማኖታችን ነው የኛ እርስት ጉልት፪
✦