ቤተ ክርስቲያንን አንተዉም ከቶ
✦
ቤተ ክርስቲያንን አንተዉም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተዉም ከቶ
ሁሉንም በሁሉ ለሚሞላው ጌታ
ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ
በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ
ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ፪
ዲያብሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ
ወጥመድ ቢዘረጋ በጒዟችን ሁሉ
እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን
አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን፪
በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት
ስለ ስሙ መኖር በስሙ መሞት
ጠላት ዲያብሎስን ምን ባያስደስት
ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ህይዎት፪
ከትዉልድ ለትዉልድ የምናስረክበው
ለልጅ ልጅ አዉርሰን ደስ የምንሰኘው
አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት
ሐይማኖታችን ነው የእኛ እርስት ጉልት፪
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተዉም ከቶ
ሁሉንም በሁሉ ለሚሞላው ጌታ
ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ
በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ
ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ፪
ዲያብሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ
ወጥመድ ቢዘረጋ በጒዟችን ሁሉ
እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን
አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን፪
በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት
ስለ ስሙ መኖር በስሙ መሞት
ጠላት ዲያብሎስን ምን ባያስደስት
ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ህይዎት፪
ከትዉልድ ለትዉልድ የምናስረክበው
ለልጅ ልጅ አዉርሰን ደስ የምንሰኘው
አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት
ሐይማኖታችን ነው የእኛ እርስት ጉልት፪
✦