ቤተክርስቲያን ቅድስት

በገዛ ደሙ የዋጃት ቤተክርስቲያን ቅድስት
እንጠብቃታለን አለብን አደራ ከውስጥም ከውጭ መከራ
የሚሰጥባት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ
ነፍሥና ሥጋ ሕይወት የሚቀድስ
በእርሷ ያለው ክብር ከሁሉም ይበልጣል
ስለ እርሷ ተግተን ልንሰራ ይገባል
ይልቅ በተሻለ አሁን ከትናንቱ
የኋዋላውን ይዘን እንሩጥ ከፊቱ
በገዛ ደሙ...............
መንፈስ ቅዱስ መርጦ አክብሯችሁ
እናንተ ጳጳሳት አድርጎ የሾማችሁ
የክርስቶስ መንጋን ተግታችሁ ጠብቁ
ተኩሏው መጥቷልና እንዳታስነጥቁ
በህይወት በምግባር ደግሞ እያበራን
በእምነት ትሩፋት እንጠብቅ ክብሯን
በገዛ ደሙ...........
የየትኛውም ዘር አይደለችም እርሷ
ለፍጥረቱ ሁሉ አንድ ነው መልሷ
ኑ ወደ እኔ ብላ እየተጣራች
የመንግስቱን ወንጌል ትሰብከናለች
እንከን የለባትም ንፁህ ነው ዘሯ
በእንክርዳድ መሃል ፍሬዋ እያበራ
በገዛ ደሙ.............
በዙርያዋ ካለው ከጠላት ከበባ
ከክህደት ወላፈን ዘወትር ከሚያደባ
በፍቅር ሆነን እየተያየን
በደም የዋጃትን እንጠብቃታለን
እርስት ነች እርሷ ለሚፈልጓት
ህይወት የምታወርስ የሰማይ መንግስት
በገዛ ደሙ...................
ዘማሪ ዲ.ን ዘማሪ ሳምሶን ነጋሽ
← መዝሙር