ቤተክርስቲያን ዘክርስቶስ

ቤተክርስቲያን ዘክርስቶስ
የጸጋው ግምጃ ቤት ማኅደረ መለኮት
የሰማይ ደጅ ነሽ የጽድቃችን ፍኖት
ምስካየ ሕዙናን ታዛ መጠለያ
በምድር የተተከልሽ የሰማይ አምሳያ
ቤተክርስቲያን ዘክርስቶስ
የማይለይሽ መንፈስ ቅዱስ
አብ በቃሉ የቀደሰሽ
ቅድስቷ ቤት አንቺው ነሽ
ከልጅነት ስልጣን ጠርተሽን በቃሉ
ከውኃ ከመንፈስ ተወልደን በስሙ
ከብረናል በቤትሽ በሥጋ ወደሙ
ኃይል ቤዛ ሆኖን ነገረ መስቀሉ
አዝ= = = = =
የአብራክሽን ክፋይ ደም እያፈሰሰ
ተመልሷል ጠላት ቀስት እየጨረሰ
ስምሽን የያዙ ተጋድሎአቸው ገኖ
ይልቅ አከበሩሽ ደማቸው ዘር ሆኖ
አዝ= = = = =
የአትናቴዎስ ስብከት የአበው ኪዳናቸው
ቤተክርስቲያን ነሽ አምባ መጠጊያቸው
እንመሰክራለን ያንቺን ልዕልና
ሠላም ለኪ እንበል ይገባሻልና
← መዝሙር