በውዳሴሽ ልትጋ

በውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ ያለው
እመቤቴ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ
ከልቤ አቀርባለሁ ምስጋና በስምሽ
መማፀኛዬ ነሽ ፅኑ ቃልኪዳንሽ
በሰላምታ ድምፅሽ ያልፀና ማን አለ
ፅንሱ በማህፀን በደስታ ዘለለ
በውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ ያለው
እመቤቴ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ
ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ
እመቤቴ ስልሽ ይቀላል ሸክሜ
ቅኔ ማህሌቱ ሰዓታት መዝምሩ
ያመሰግኑሻል ምድርና ጠፈሩ
በውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ ያለው
እመቤቴ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ
እናቱ ነሽና አንቺ ለአዶናይ
ማለድኩሽ ከፊትሽ ይቅርታውን እንዳይ
ሰዓሊለነ ብዬ ይኸው ተርፌያለሁ
ባንቺ ተደግፌ ነገም እኖራለሁ
በውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ ያለው
እመቤቴ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ
ነይ ነይ እልሻለሁ እንደ ካህናቱ
በሰዓታት ፀሎት ቆሜ በሌሉቱ
ዝም አልልም እኔ አወድስሻለሁ
የዓለምን መከራ እረሳብሻለሁ
← መዝሙር