በዘር አንድ የሆነው

በዘር አንድ የሆነው ሌዋዊው ትቶኛል
ባዕዱ ሳምራዊ ከሞት አድኖኛል
በቁስሌ ላይ ዘይት የሚያስ ፍቅረኛ
የሰላም ሰው ስጠኝ ሁነኛ ጓደኛ
ከማይጠፋው ትውልድ ስለተወለድን
አይቀርም እመኑ በምድር ዘራችን
ከእግዚአብሔር ተወልደን ልጆች ተብለናል
ባሮች አይደለንም ነጻነት ወጥተናል
አንተን የሚመስል ቀናና የዋኅ ሰው
ወንጌልኽን ነገረኝ ሕይወቴን ለወጠው
ዓለም የሰጠችን ሞት ነበረ ድሮ
ክርስቲያን አዳነኝ ወንጌልን አስተምሮ
በሥጋና በደም የማልዛመደው
በክርስቶስ ጥምቀት ዘሩ ከእኔ ጋር ነው
ጓደኛዬ እርሱ ነው ሕይወት የሚሰጠኝ
በቃሉ በፍቅሩ ተመስጫለሁኝ
ልቡ ቅን የሆነ ጓደኛ መርጬ
ሰላሜ ልዩ ነው ዛሬ ተለውጬ
ክርስቲያን በሙሉ በዚህ ያስ ውቃል
ፍቅሩ ይለውጣል ሥራው ይማርኝል
ከዓለም ጉድጓድ ውስጥ መስዬ ወድቄ
ይኸው ሰላም ሆንኩኝ ከአምላከ ርቄ
እውነተኛ ፍቅር አስተማረኝና
አዲስ አደረገኝ እኔን ክርስትና
← መዝሙር