ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ

ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ
ለስልሶላት ነበር ሀይማኖት መሬቱ
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ
ተለቅሞላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ
ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች
ተካይዋ በምግባር ስላላስደሰተች
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ
ሌሎች እንዳይጠፉ ከእርሷ የተነሳ
ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት
ጠባቂ መላእኳዋ ተማጸነላት
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት
ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች
← መዝሙር