ብርሃን ወጣ

ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ የሚያንጸባርቅ
የአምላክና የሰው ልጆች እውነተኛ እርቅ
ደስ ይበለን በመስቀሉ ብርሃን
እልል እንበል በአንድነት ሆነን
ድነት ሆነ ለመላው ዓለም
ከፊት ለፊት በመሳሉ የመስቀሉ ነገር
የሚወደው ሐዋርያ የወንጌል መምህር
ዮሐንስም ስቅለቱን በማየቱ
ሲያዝን ኖረ በምድራዊ ሕይወቱ
ቢያሰቅቀው ሞቱ ግርፋቱ
አዝ . . .
ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው
በዓለም ጥበብ ለሚኖሩት እውነት ተስኗቸው
ለጠቢብ ሰው በመንፈስ ለሚኖረው
የመዳን ቀን እውነተኛ አርማ ነው
ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው
አዝ . . .
እስከ መስቀል ላልተለየው ቅዱስ ሐዋርያ
ለዮሐንስ የወንጌል ሰው የፍቅር ባለሞያ
ምስጋናችን ከምድር ይድረሰው
እንድናለን በሰጠን ምሳሌው
ሰ−ች ሁሉ እንከተለው
አዝ . . .
← መዝሙር