ብርሃን የለበሰው

ብርሃን የለበሰው በሰማያት ያለው
እንደ እግዚአብሔር ከቶ ማንም የለም
ውኆችን በእፍኙ የሠፈረ
ተራሮችን በሚዛን የመዘነ
ሰማይን በስንዝር የሚለካ
ዘመንን በዘመን የሚተካ
አዝ ---
ከዓለም በፊት የነበረ
ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ
በምድር ክብብ የሚቀመጥ
ሁሉን ሲለውጥ የማይለወጥ
አዝ ---
ዙፋኑ የጸና በሰማይ
ሁሉ የሚቻለው አዶናይ
ለመንግሥቱ ፍጻሜ የሌለው
አልፋና ኦሜጋ አምላክ ነው
አዝ ---
ከሀሊ ኩሉ ሁሉንም የሚያውቅ
ፈታሄ በጽድቅ ሥራው ረቂቅ
ዓለምን የመላ ፈጥሮ የሚገዛ
መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ
← መዝሙር